ጥቅስ፣ „Femmes-Tische ከዚህ በፊት ተዘግተዉብኝ የነበሩትን በሮች ከፍቶልኝ ብዙ ነገር እንዳዉቅ ረድቶኛል“
በዚህ ውይይት ላይ የተሳተፈች ሴት.
amharique
የ Femmes-Tische እና Hommes-Tische (የሴቶችና የወንዶች መገናኛ ጠረጴዛ) በሚባለዉ ዝግጅታችን ላይ ለመካፈል ስለመጡልን ልባዊ ሠላምታችን ይድረሳችሁ። በዚህ የዉይይት ዙሮች ወይም መድረኮች ላይ ከሌሎች ሰዎች ጋር ይገናኛሉ። እነዚህን ሰዎች በራስዎ ቋንቋ ጠቃሚ የሆኑ ስለ አስተዳደግ፣ ስለ ጤንነት እና ስለ ዉህደት ጥያቄዎች ላይ ይወያያሉ። ቋንቋና ማንነትን ሳይለዩ እነዚህ የዉይይት መድረኮች ፍላጎት ላለዉ ሰዉ ሁሉ ክፍት ናቸዉ።
. በትንንሽ ግሩፖች ወይም ሰበስቦች ይካሄዳሉ
. የሚመሩት የእርስዎ ቋንቋን በሚናገር ሰዉ ነዉ
. ላይ ሌላ ሰዉ ለመተዋወቅ ይችላሉ
. ለእለት ተእለት ህይወትዎ የሚፈልጉት ድጋፍ ና ሐሳብ እዲሁም ጠቃሚ መረጃዎችን ይሰጣሉ
. የሚደረጉት በሚኖሩበት አካባቢ ወይም በጎረቤትዎ ነዉ
. ከክፊያ ነጻ ናቸዉ
. ያዝናኑኦታል
በእነዚህ የዉይይት መድረኮች ላይ ከ 6 እስከ 8 ሰዎች ይካፈላሉ። ወንዶችና ሴቶች በተለያዩ የመወያያ መድረክ ላይ በአንድ ግለሰብ ቤት ወይም በሕዝብ ተቋማት ለምሳሌ በቤቴሰብ ማዕከል ወይም በት/ቤት ዉስጥ ነዉ። ስብሰባዉን የሚመሩ ሰዎች የተለያዩ ማህበራዊና ባሕላዊ አላቸዉ። ስብሰባዉ የሚካሄደዉ በራስዎ ቋንቋ፣ በጀርመንኛ ወይም በኢንግሊዚኛ ነዉ። የመወያያ ርዕስ በፊልም ወይም በፎቶ መልክ ይቀርባል። ከዚያ ላይ በመነሳት ዉይይት ይደረጋል። ምስጋና ለመረጃዎችና ለልምድ ልዉዉጡ የዉይይቱ ተካፋዮች ለእለት ተእለት ህይወታቸዉ የሚፈልጉት ድጋፍ ና ሐሳብ ያገኛሉ። በሻይ እረፍት ላይ ከሌሎች ሰዎች ጋር በጥሩ ሁኔታ መተዋወቅ ይችላሉ።
. ሕጻናትን በጥሩ ሁኔታ ድጋፍ መስጠት
. በአስተዳደግ ዙሪያ ድንበር የሚያስፈልጋቸዉ ጉዳዮች
. በብዙ ቋንቋ በማደግ ዙሪያ
. የትምህርት ሥራዓትና የሙያ መረጣ በስዊዘርላንድ
. ሱሰኝነትን በቅዲሚያ በቤቴሰብ ማስወገድ
. ታዳጊ ወጣትነት
. የተለያዩ ሜዲያዎች አጠቃቀም
. ጤነኛ መሆን፣ በጤንነት መቆዬት
. ጤናማ አመጋገብ ና እንቅስቃሴ
. በራስ መተማመንን ማጠንከር
. የበጀት አመዳደብ
. የሕይወት ዋስትናን መረዳት
. በጥሩ ስሜት ላይ መገኘትና ሚዘናዊነት
. እርጅና በስዊዘርላንድ